WE STRONGLY CONDEMN THE VIOLENCE AGAINST THE CHIEF OF STAFF OF  ETHIOPIAN ARMED FORCES, GENERAL SEARE MEKONNEN, AMHARA STATE PRESIDENT, DR. AMBACHEW MEKONNEN AND THEIR COLLEAGUES. THIS IS AN ACT OF TREACHERY. 

Press Release
Articles
Demo 22 March 18 London
We are one!
Emperor Tewodros
Emperor Yohannes IV
Emperor Menilik II
Fitawrari-Habtegiorgis
Lt/General Jagema Kelo
massive-protest-currently-underway-in-gondar-146994254984gkn
Supporting Our Airforce
Show More
Lt.Mola Abate – An Ethiopian Hero and founder of  TEDUF

Read on Getachew Yesefa- another hero who paid the ultimate sacrifice in our struggle against oppression and treachery 

Read more - Click Here

1/15
 
df31312b1e90443589d625acb5c29f17_18
Oromo-protest
_MG_3491-b-1100
massive-protest-currently-underway-in-gondar-146994254984gkn
ethiopia_farmer_threshing_wheat
334847_Ethiopia-rally
ethiopia-45
EthioPrincesses
16292_1343157087175
_90881136_mediaitem90881135

14 Mar 2020

ድክመቶችን በጊዜ ካላረምን አባይን በአንድነት መታደግ አይቻልም!

አንዳንዶች ግብፅ ለማስፈራራት ነዉ እንጂ ጦርነት ዉስጥ አትገባም ይላሉ። የዉስጥ 5ኛ ረድፈኞችን በገንዘብና በመሳሪያ እያስታጠቀች አገር የማፍረስ ሙከራዋን ታደርጋለች እንጂ ለማያዛልቃት ጦርነት አትጀምረዉም ይላሉ። እንደኛ አስተያየት ይህ አመለካከት ሁለት ነገሮችን ያገናዘበ አይመስልም። አንደኛ፣ የአባይ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የበፊቱ ሁኔታ የተመሰረተበት አስተሳሰብን ቀይሮት በነሱ አነጋገር “የሞት የሽረት” አድግጎታል። ሁለተኛ፣ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል በዓለም አቀፍ መድረክና ፊት ይህ አይነት ተፋጠጥ፣ ማለትም ሁለቱም ወገኖች በአሽናፊነት (በዊን፟፟-ዊን መፍትሄ) ካልተወጡት፣ አንድ ወገን ተሽንፎ ከፍተኛ የፖለቲካ ቀዉስን በአገሩ የሚያስከትልበት ሁኔታ፣ ተፈጥሮ አያዉቅም። በአጭሩ ወይ ጠ/ሚ አበይ ወይ ፕረዚዳንት ሲሲ ሰለባ ይሆናሉ፣ ስለዚህ ሲሲ ጦርነት የመክፈት እድሉ ከበፊቱ ከፍ ያለ ነዉ ብሎ መገመት አግባብነት ይኖረዋል። ባይሆንም እንኳ አባቶቻችን እንደሚተርቱት “አይሆንንም ትተሽ፣ ይሆናልን ያዢ” ነዉና ለጦርነት መዝጋጀት የግድ ነዉ። ማዘናጋትና ማታለል የጦርነት ከፍተኛ ዘዴ በመሆኑ ለሁሉም አይነት ጥቃት፣ በአየርም ይሁን በምድር፣ግድቡን ከማፍረስ እስከ መንግሥት መቀየር ሊሄድ ስለሚችል፣ መዘጋጀት ይገባል እንላለን። 

11 Jul 2019

‘አመራር ያጣ ትግል፣ ተቀባይ ያጣ ድል’

የዛሬ ዓመትም የጭቆናው በላይ በላይ መከመር ያማረረዉ ሕዝባችን ከፍተኛ መስዋአትነት ከፍሎ ያመጣዉ እልል የተባለለት ለዉጥን ሁላችንም እናዉቀዋለን። ታዲያ ‘አመራር ያጣ ትግል፣ ተቀባይ ያጣ ድል’ ሆነናም ፈረንጆቹ ‘በፖለቲካ ዓለም ዉስጥ ሳምንት ረጅም ጊዜ ነዉ’ እንደሚሉት ዛሬ ደግሞ ግራ የተጋባ ሁኔታ ዉስጥ ወድቀናል።

 

ከበፊቱ በበለጠ ተከፋፍለን መደማመጥ እንኩዋን ተስኖን ፣ የጥላቻ ግርዶሽ በክልሎችና ቡድኖች ነግሶ፣ በበለጠ የመጠፋፋት ጎዳና ላይ እንገኛለን። ለዚህም ስኔ 15 ቀን 2011 በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና በፌደራል መንግሥት መቀመጫ የታዩት ክስተቶች የተጀመረውን የተሐድሶ አቅጣጫ የሚያስትና ሌሎች መዘዞችንም የሚመዝ አደገኛ ክስተት ነው። ይህንንም ሁኔታ ለመቀየር በደንብ የታሰበበትና ፈጣን እርምጃዎች ካልተወሰዱ ወደፊት የሚጠብቀንን መከራ በጥቂቱ እያመላከተን ነዉ ለማለት ይቻላል። በዚህ ክቡር የሆነዉ የሰዉ ነብስ በጠፋበትና በተለይም ደግሞ በመሪነት ደረጃ ብዙ ሥራ እንደሚሰሩ ታምኖባቸዉ የነበሩ ሰዎች በከንቱ መቅረት፣ ታጠቅ ኢትዮጵያ የተሰማውን ልባዊ ሀዘን ለተጎጂ ቤተሰቦች፣ለኢፌዲሪ መንግሥት፣ ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይገልጻል።

22 Sep 2018

ሁሉንም ሃይሎች ያካተተ ብሄራዊ ጉባኤ ይጠራ! የሁሉም ዜጎች የህይወት ዋስትና ነዉና!

ክቡር ጠ/ሚ አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጀምሮ በብሄረሰቦች መካከል እና አብዛኛዉን ጊዜ በተመረጡ ብሄረሰብ አባላት ላይ ያነጣጠረ ጥቃቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

የሰሞኑ የቡራዩ እና አዲስ አበባ ዙሪያ ጭፍጨፋ እና ኢሰባዊ ድርጊቶችም የዚሁ ተቀጥያዎች ናቸው። ይህ በደቡብ ኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ለየት የሚያደርገው ከመንግስት መቀመጫ አፍንጫው ስር ከመፈፀሙም በላይ ለሁለት ቀናት የዘለቀ የመንግስት እርምጃ መዘግየት የታየበት መሆኑ ነው።

በታጠቅ እምነት የየክልል የፀጥታ ተቋማት ወገንተኝነታቸው ለፍትህ፤ለህግ የበላይነት እና ሙያዊ ግዴታቸው ሳይሆን የኛ ለሚሉት ብሄር አባላት ይመስላል።የነሱ የሚሉት ብሄር አባላት ለሚፈፅሙት ወንጀል በቀጥታም ይሁም በተዘዋዋሪ ተባባሪ ሲሆኑ ይታያል። መንግስት እየፈፀማቸው ያሉ ሀገራዊ አና አሁጉራዊ ጉዳዮች እንዳሉ ሁነው የዜጎችን በህይወት የመኖር፣በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የመኖር ፣ሀብት እና ንብረት የማፍራት ፣እና ሌሎችም ዱሞክራሲያዊ እና ህገመንግስታዊ መብቶችን ማስጠበቅ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል።

በታጠቅ ኢትዮጵያ እምነት የፌዴራል እና የክልል የፀጥታ ተቋማት ሙሉ በሙሉ የተጀመረውን ለውጥ የመጠበቅ ፍላጎት እና ቁርጠኝነት አያሳዩም።

 

.............አሁንም የሁኔታዎች መባባስና ወደ አልሆነ አቅጣጫ መሄድ እንዳይከተል፣ በአንድ ሰዉ ዙርያ የተደራጀ የትግል ጉዞ አንደ እንቧይ ካብ የመፍረሱ ዕድል ከፍተኛ ነዉና ፣ ሁሉን ያቀፈና ተጠያቂ የሚያደርግ፣ ብሄራዊ የአንድነት መንግስትንም አንደ አንደ አማራጭ የሚያካት፣ ብሄራዊ ጉባኤ ማድረግ ቅድሚያ ሊሰጠዉ የሚገባ ጉዳይ መሆኑን መንግስትን አጥብቀን ልናሳስብ እንወዳለን።
 

11 Aug 2018

ታጠቅ ኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግሉን ተቀላቀለ

ነሐሴ ፪ ፳፲ የድርጅቱ ምክር ቤት የሚከተለዉን ዉሳኔ አስተላልፉአል።

ታጠቅ ድሮዉንም ሁለገብ የትግል ስልት የመረጠዉ ቅድመ ለዉጥ የነበረዉ ገዥው የኢሕአዴግ ቡድን ለሰላማዊ ትግል የሚሆን ተክለ ሰዉነት ያልነበረዉ በመሆኑና ተገፍተንና ተገደን ይህን የትግል ስልት የመረጥን በመሆናችን አሁን ግን ባለዉ ነባራዊ ሁኔታ ለሰላማዊ ትግል ሊሆን የሚችል ጅማሮ በመኖሩና ይህን የሰላም ሂደት ማጠናከር፣ የተከፈተዉንም የሰላማዊ ትግል መድረክ ማስፋትና የበኩላችንን መወጣት ስላለብን ከነሐሴ ፪ ፳፲ ጀምሮ በይፋ የትግል ስልታችን ሰላማዊ እንዲሆን ወስነናል። ይህንንም ገቢራዊ ለማድረግ ቆርጠን እንታገላለን።

02 Jul 2018

አገራዊ ጥቅምን ማስቀደም ከሃቀኛ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ የሚጠበቅ ተግባር ነዉ

የታጠቅ ኢትዮጵያ ሥራ አስፈጻሚ ሰኔ 19 2010  ባደረገዉ መደበኛ ስብሰባ የወቅቱን የፖለቲካ ሁኔታ በጥልቀት ገምግሟል። በሰኔ 16 በአዲስ አበባ ላይ በፍቅርና አብሮነት ላይ የተቃጣዉን ጥቃትም አቅም በፈቀደ በሰብሳቢዉ መረጃ ላይ በመንተራስ በሁኔታዉ ላይ ዉይይት አካሄዷል። በዚህም መሰረት፡

1ኛ በአሁንኑ ሰአት ከራሱ ከኢህአዴግ ዉስጥ የወጣዉ የለዉጥ ሃይል የህዝቡን ጥያቄ በስፋት የተረዳና መፃኢ ኢትዮጵያን ህልዉና የተሻለ ለማድረግ ከተቃዋሚዎች ጋር ሁሉን አቀፍ ሽግግር ለማድረግ የሚያስችል ዝግጁነት ያለዉ የለዉጥ ቡድን መሆኑ ግንዛቤ ተወስዷል።

2ኛ ታጠቅ ላለፉት በርካታ አመታት በዋናነት የትግል ማእከሉን ያደረገበት የአጭር ጊዜ ግቡ ኢትዮጵያን ከተጋረጠባት የህልዉና አደጋ መታደግ ነበር። በዚህ ረገድ ታጠቅ ይህ በዶ/ር አብይ የሚመራዉ የለዉጥ ቡድን ይህንን መሰረታዊ ችግር በመረዳት ኢትዮጵያችን ላይ ተጋርጦባት የነበረዉን መሰረታዊ ችግር በመፍታት እረገድ እሰየው የሚያስብል ስራ መስራቱን በጥልቅ ተገንዝቧል።

07 Apr 2018

አለባብሰዉ ቢያርሱ በአረም ይመለሱ!

አገራችን ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት በፀረ-ዴሞክራሲያዊ አገዛዞች የምትማቅቅ አገር ናት። ዛሬም ዜጎቿ መብትና ጥቅማቸዉን በሕጋዊና ሠላማዊ መንገድ ለማስከበር እልህ አስጨራሽ ፈታኝ ጊዜ ላይ ናቸዉ። የአገራችን ሕዝብ ላለፉት ሶስት ዓመታት ትግሉን ከአድማስ አድማስ በማስፋት የተሻለ ተጽእኖ መፍጠር የቻለ ጠንካራ ትግል በማድረጉ፣ ይህን ተከትሎ በአፋኙ ስርዓት በራሱ ዉስጥ ጎራ መፍጠር የተቻለ ትግል እስከመሆን በቅቷል። ይህ የሕዝብ ብሶትና ጥያቄ ተገቢነት አለዉ የሚል ሃይል በገዥዉ ኢሕአዴግ ዉስጥ ከመፈርጠም አልፎ የአመራር ሚናን መጨበጥ ችሏል። በዉጤቱም አዲስ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ብሎም የጠቅላይ ሚንስትር ሹመት ፀድቋል።

1 / 5

Please reload

UPDATES

በሜቴክ ባለስልጣናት ላይ በዶ/ር አብይ መንግስት ስለተወሰደዉ ጸረ ሙስና እርምጃ

 

በስተሰሞኑ ሜቴክ ባለስልጣናት ላይ በዶ/ር አብይ መንግስት የተወሰደዉ ጸረ ሙስና እርምጃ ወቅታዊ ሲሆን በየመንግስት አካላትና ማህበረሰባችን ዉስጥ የተሰገሰጉትን ወንጀለኞች ወደ ሕግ ማምጣቱ ቀጣይነት ያለዉ ጉዳይ መሆን እንዳለበት በአጽንኦት እየገለጽን ለዚህም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሙሉ ትብብር እጅጉን አስፈላጊ በመሆኑ በቀና ህሊናና ፍጹም ሀገር ወዳድነት ሙሉ ትብብር እንድናደርግ እናሳስባለን። 

በሌላ አንጻር ጸረ ሙስና እርምጃዉ በአንድ ሕዝብ ላይ የተነጣጠረ አድርገዉ ለማወናበድና ለወንጀላቸዉ የፈረደበትን ሕዝብ ከለላ ለማግኘት የሚጥሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ሊኖሩ ስለሚችሉ ይህ ሐሰት መሆኑን ተረድተን የወንጀለኞች ከህብረተሰባችን መጥፋት የመላ የኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነትና ጥቅም መሆኑን አዉቀን ሌሎችንም ለማሳወቅ ጥረት ማድረግ እንዳለበን በተጨማሪ እናሳስባለን 

ህዳር ፭ ፳፩፩

Stop the New Wave of Ethnic Attack on Amharas!

”The Ethiopian government must intervene to protect thousands of ethnic Amharas who are on the verge of displacement due to violent attacks on their homes by ethnically-motivated youth groups in Oromia Regional State. Oromo youth groups this week surrounded Amhara homes, beating residents, and looting property in the Siyo District of Qellem Wollega Zone, Oromia State. At least 20 Amharas have been killed in such attacks since October 2017 but residents say the authorities have done nothing to stop them”. Amnesty International reported on 8 June 2018

የዶ/ር አብይ አህመድ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት መመረጥ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትርጉም የሚኖረዉ በተለይ የጦር ሃይሉንና ደህንነቱን ሙሉ በሙሉ መለወጥ የሚያስችል ስልጣን ሲኖረዉ ብቻ ነዉ።   

28 March 2018

ታጠቅ ለነፃነት​

Can you support the cause?

Tatek Movement

Emperor Yohannes IV